አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እየተካሄደ ያለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ነው አሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ተዘዋዋሪ ታዛቢ።
በምዕራብ ሸዋ ዞን የኦነግ ተዘዋዋሪ ታዛቢ ሚልኬሳ ህርኮ እንዳሉት÷ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ምርጫ ያለምንም ተግዳሮት በነጻነት በመዘዋወር እየተመለከቱ ይገኛሉ።
ሕዝብ ያለምንም እንግልት እየመረጠ እንደሚገኝ መመልከታቸውንም ገልጸዋል።
ፓርቲያቸው በምርጫ ሲሳተፍ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን አንስተው÷ ይህ ዕድል ተፈጥሮ ፓርቲያቸው መካፈል መቻሉ የፖለቲካው ምህዳር መስፋቱን እንደሚያሳይ አስረድተዋል።
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision.