የሀገር ውስጥ ዜና

የጌዴኦ አባ ገዳ ቢፎሚ ዋቆ ድምፅ ሰጡ

By Abiy Getahun

June 01, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጌዴኦ አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ በዲላ ከተማ ወናጎ ምርጫ ክልል 2 ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ የሀገርን ልማት በማረጋገጥ እና ሰላም በማስጠበቅ ኢትዮጵያን ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይመራል ያሉትን ፓርቲ መምረጣቸውን ተናግረዋል። ‎ ሕብረተሰቡ ለሀገር ይጠቅማል የሚለውን እንዲመርጥም ጥሪ አቅርበዋል። ‌‎ ‎በኢብራሂም ባዲ

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision