አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአፋር ክልል ነጻ እና ሰላማዊ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል አለ የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ምርጫው በክልሉ በሚገኙ 32 የምርጫ ክልሎች ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቅቋል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሀንፈሬ ዓሊሚራህ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ክትትል የሚያደርጉ ግብረ ኃይሎች ተቋቁመው ሂደቱ ሲገመገም መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
ሕዝቡ ስለ ምርጫ ያለው ግንዛቤ እና ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
የምርጫ ሂደቱ ከቀደሙት ዓመታት የተሻለና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የመግባባት መንፈስ የሰፈነበት እንደነበር የጋራ ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡
ተግዳሮቶችን ለመፍታት ቀድሞ የተደረገው ዝግጅት ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ማድረጉም ነው የተገለጸው፡፡
የሕዝቡ ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያበረታታ መሆኑን የገለጸው ምክር ቤቱ፥ ምርጫው በተፎካካሪ ፓርቲዎች ተቀባይነት ማግኘቱ ሒደቱ ስኬታማ እንዲሆን ማስቻሉን አመልክቷል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን በመግለጽ፥ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ሳይበገሩ ድምፃቸውን ለሰጡ ዜጎች ምስጋና ቀርቧል።