አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት እየተለጠፈ ሲሆን መራጮችም ውጤቱን እየተመለከቱ ነው፡፡
በዚህም በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ቡሬ፣ ሐይቅ፣ ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ እና ቻግኒ ከተሞች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡
በተጨማሪም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ምርጫ ክልል፣ በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ በሊበን የምርጫ ክልል በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራው ተጠናቅቆ ጊዜያዊ ውጤት እየተገለጸ ነው። ነዋሪዎችም በየምርጫ ጣቢያዎች የተለጠፈውን ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት እየተመለከቱ ይገኛሉ።
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavoted #Democracy #fanatelevision