የሀገር ውስጥ ዜና

የሀገር ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት ማምረት ስንችል ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

By Melaku Gedif

June 03, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነትና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው ብለዋል፡፡

መንግሥት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የታለመውን ዘላቂ ዕድገት እና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን አሻሽሏል፤ አሠራሮችን ዘርግቷል፤ ማበረታቻዎችን አድርጓል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዚህ ሪፎርም አካል የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፍሬው በግልጽ እየታየ እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡