የሀገር ውስጥ ዜና

ዜጎች በነፃነት ድምጽ መስጠታቸውን ተመልክቻለሁ – የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን

By Abiy Getahun

June 03, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዜጎች በነፃነት ይበጀኛል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጽ መስጠታቸውን ተመልክቻለሁ አለ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን።

ፌዴሬሽኑ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ውስጥ በተሰጠው የታዛቢነት ኃላፊነት መሰረት በተለያዩ አካባቢዎች ያከናወነውን የምርጫ ሂደት ክትትልና ምልከታ ማጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ተወካይ አሌክሳንደር ንጉሴ በወቅቱ እንዳለው÷ በምርጫው 32 ሺህ 500 ወጣቶች በታዛቢነት፣ በአስተባባሪነት ደግሞ 2 ሺህ 500 ወጣቶች ተሰማርተዋል።

ወጣቶች በምርጫው ወቅት የነበራቸው ተሳትፎ ለምርጫው ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል ነው ያሉት።

ፌዴሬሽኑ በታዛቢነት ሚናው የምርጫ ግብዓቶች በተገቢው መንገድ መሟላታቸውን አንስቶ፤ ዜጎች በነፃነት ይበጀኛል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጽ መስጠታቸውን ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተወዳደሩ ፓርቲዎችም በድህረ ምርጫ ወቅት ውጤትን በፀጋ በመቀበል ለወጣቱ የማህበረሰብ አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባም አስገንዝቧል።

በሔብሮን ዋልታው