አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ34ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር በዛሬ ዕለት ይደረጋል፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ከነገሌ አርሲ ተስተካካይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረግ መርሐ ግብር ተይዞሎት የነበረ ቢሆንም በዕለቱ በአዲስ አበባ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ጨዋታ አለመደረጉ ይታወሳል፡፡
በዚህም በተስተካካይ መርሐ ግብር ጨዋታው በዛሬው ዕለት እንዲደረግ አክሲዮን ማህበሩ መወሰኑ ይታወቃል፡፡
ሊጉን ሲዳማ ቡና በ61 ነጥብ ሲመራው መቻል 53፣ ነገሌ አርሲ 52 እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ በ48 ነጥብ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
አቤል ያለው በ14 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ ሲመራው ናትናኤል ዳንኤል በ13 ግቦች ይከተላል፡፡