ቢዝነስ

አየር መንገዱ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ይፋ አደረጉ

By Hailemaryam Tegegn

June 04, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር አዲስ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ይፋ አድርገዋል።

የክፍያ ካርዱ ደንበኞች በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነው በቀላሉ ግብይት እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነው።

በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ አባላት የሆኑ መንገደኞች በሚደርሱበት ማንኛውም የዓለም መዳረሻ ፈጣን፣ ቀላልና አስተማማኝ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ያስችላል።

ካርዱ አስተማማኝ የደኅንነት ጥበቃ ሥርዓት ያለውና የሦስቱንም ተቋማት ዓርማና ምልክት በአንድ ላይ የያዘ መሆኑም ተገልጿል፡፡

አዲሱ ዓለም አቀፍ የግብይት ካርድ ለደንበኞች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እና ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያስገኝ ሲሆን፥ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች ክፍት መሆኑም ነው የተገለጸው።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በየጉዟቸው የሚያደርጉት ግብይት ተጠራቅሞ ወደ ጉዞ ዕድል የሚቀየር ሲሆን፥ ካርዱን በሽያጭ ማሽን ወይም በኢ-ኮሜርስ አማካኝነት ለኦንላይን ግብይት በሚጠቀሙበት ወቅት ለተጨማሪ ሽልማት የመታጨት እድላቸውን የሚያሰፋ ነው፡፡