አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ከንቲባ አምባሳደር አሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ ÷ በአምባሳደር አሊ አብዶ ሕልፈተ ሕይወት ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
ከንቲባዋ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
አምባሳደር አሊ አብዶ 27ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በመሆን እንዲሁም በሱዳንና ናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡