አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አዲስ የምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሾመ።
ምክር ቤቱ ባካሄደው 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ አዳዲስ ሹመቶችን አፅድቋል።
በዚህ መሰረት ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህን የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ለክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት የቀረቡትን የወይዘሮ ሚስራ አብደላ ሹመትንም በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
በተጨማሪም ወይዘሮ ፎዚያ በክሪ የህግ፣ አስተዳደር የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ተሾመዋል፡፡
እንዲሁም አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን በምክር ቤቱ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ሾሟል፡፡
በተሾመ ሃይሉ