አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሰባት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ወደ ፒዮንግያንግ ያቀኑት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በቤጂንግ በተቀበሉ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ሺ ጂንፒንግ በሰሜን ኮሪያ ቆይታቸው ከሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተለይም በኒውክሌር፣ ከአሜሪካ ጋር ባላቸው ግንኙነት እንዲሁም በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለውን ግጭት መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተመላክቷል፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ወደ ፒዮንግያንግ አቅንተው እንደነበር ይታወሳል።
በብርሃኑ አበራ