አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አካል የሆነውን የክልሉን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በብቃት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።
ማዕከሉ 4 የፌዴራል እና 6 የክልል ተቋማት አገልግሎትን በአንድ ጣሪያ ስር በማጣመር ከ15 በላይ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አመላክቷል።