አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አባትና ልጅ የሆኑት ሊሊያን ቱራም እና ማርከስ ቱራም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን በተለያዩ ጊዜያት በዓለም ዋንጫ መወከል ችለዋል፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በፈረንጆቹ 1998 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሲሆን ÷ ትልቅ አስተዋፅኦ ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ አባት ሊሊያን ቱራም ነበር። የአባታቸውን ፈለግ የተከተሉት ልጆቹ ማርከስ እና ኬፍራን ቱራም እግር ኳስን በታላቅ ደረጃ እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡
የኢንተርሚላን የፊት መስመር ተጫዋቹ ትልቁ ማርከስ ቱራም እንደ አባቱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን የመወከል እድልን አግኝቷል።
በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ የነበረው ማርከስ ቱራም በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ለሻምፒዮንነት ከተገመቱ ብሔራዊ ቡድኖች አንዱ በሆነው የዲዲዬ ዴሾ ስብስብ አካል ሆኖ ሰሜን አሜሪካ ይከትማል።
የማርከስ ቱራም ታናሽ ኬፍራን በጣሊያን ሴሪ ኤ በዩቬንተስ ጥሩ የሚባል ጊዜ ቢያሳልፍም፥ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾን ማሳመን ባለመቻሉ ሳይመረጥ ቀርቷል።
በሙባረክ ፈንታው