የሀገር ውስጥ ዜና

አዲሱ የግብር ከፋዮች ምደባ በአዲሱ በጀት ዓመት መተግበር ይጀምራል

By Melaku Gedif

June 10, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲሱ የግብር ከፋዮች ምደባ ከአዲሱ በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል አለ የገቢዎች ሚኒስቴር፡፡

የ2019 በጀት ዓመት የታክስ ከፋዮች የደረጃ ምደባ ኮሚቴ ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ሪፖርት አቅርቧል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ አዲሱ ምደባ ግብር ከፋዮች ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

የሚኒስቴሩን ተደራሽነት ለማጠናከር እንዲሁም የግብር ከፋዮችን አደረጃጀት ለማስፋት እንደሚያስችልም አመልክተዋል፡፡

የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመው ÷ለተግባራዊነቱ የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ምደባው ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን መሠረት አድርጎ የተከናወነ ሲሆን÷ ለግብር ከፋዮች ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት የሚሰበሰበውን ገቢ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

አዲሱ የግብር ከፋዮች ምደባ ከአዲሱ በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡