ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአፍጋኒስታን በጎርፍ አደጋ የ160 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

August 29, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍጋኒስታን በዚህ ሳምንት በደረሰ የጎርፍ አደጋ በትንሹ የ160 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በአሁኑ ጊዜም የነፍስ አድን ሰራተኞች በጭቃ ውስጥ እና በህንፃዎች ፍርስራሽ ስር የጠፉ ሰዎችን እያፈላለጉ መሆኑም ነው የተነገረው።

በጎርፍ አደጋው በአፍጋኒስታን ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ 13 ግዛቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን፥ በርካታ መኖሪያ ቤቶችም በጎርፍ አደጋው መወሰዳቸውን የሀገሪቱ የአደጋ አመራር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከአንፋኒስታኗ ዋና ከተማ ካቡል በስተሰሜን በምስትገኘዋ ፓርዋን ብቻ በጎርፍ አደጋው የ116 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ 120 ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ፤ 15 ሰዎች ደግሞ የገቡበት አልታወቀም።

የአፍጋኒስታን የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ በአሁኑ ወቅትም የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት የተጎዱ ሰዎችን በማቋቋም እና ምግቦችን በማከፋፈል ስራ እየሰሩ ነው።

ምንጭ፦ aljazeera.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።