አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ፣ በአማራ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም በሶማሌ ክልል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለክልሎችና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩ እጩዎች ውጤቶችን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጋቸው 22 የፀደቁ ውጤቶችን ነው።
በአማራ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1፣ በኦሮሚያ ክልል ለክልል ዕጩ 9 ለተወካዮች ምክር ቤት 7 ውጤቶችን ነው ይፋ ያደረገው።
በተመሳሳይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3 የፀደቁ ውጤቶችን ይፋ አድርጓል።
በዙፋን አምባቸው