አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዛሬ ጀምሮ አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ መሰጠት ጀምሯል።
የከተማዋ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዘገየ በላይነህ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ከሴኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አዲሱ ሰሌዳ ለከተማዋ ተሽከርካሪዎች መሰጠት ተጀምሯል።
በዚህ መሰረትም ተመዝግበው ሲጠባበቁ የነበሩ አሽከርካሪዎች በተመዘገቡበት ቅርንጫፍ በኩል ስልክ ተደውሎ እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።
አዲሱ ሰሌዳ የሚሰጠው ለአዳዲስ ተሽከርካሪዎች ብቻ መሆኑንም ነው ዋና ሥራ አስኪያጁ ያስገነዘቡት፡፡
ነባሩን የተሽከርካሪ ሰሌዳ የሚጠቀሙትን በተመለከተ ወደፊት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በኩል ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡
በመሳፍንት እያዩ