አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የድህረ ምርጫ ሥራዎችን በስኬት በመፈፀም የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን። በክልሉ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አፈጻጸም እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ ተካሂዷል። አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ አንዳንድ የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች ተባብረው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሒደት እንዲደናቀፍ ተንቀሳቅሰው ነበር። ሕዝቡ እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የላቀ ተሳትፎ በማድረጋቸው የምርጫውን ሒደት ለማደናቀፍ የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል።
በዚህ የጋራ ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለተወጡ በሙሉ ምሥጋና ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ አመላክቷል። በቀጣይም በየዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ወደ ላቀ ከፍታ ለመድረስ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።