የሀገር ውስጥ ዜና

የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

By Yonas Getnet

June 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የሐዋሳ ሐይቅን ተፈጥሯዊ ውበት ከዘመናዊ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ጋር በማሰናሰል ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃል።

የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ማስተር ፕላን 12 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ÷ የመጀመሪያው ዙር ግንባታ ከፍቅር ሐይቅ የሚጀምር ይሆናል።

በ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው ፕሮጀክቱ ÷ ባለ ሃብቶችን እና የከተማዋን ነዋሪዎች እንደሚያሳትፍ ተመላክቷል፡፡

ፕሮጅክቱ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን ÷ የመጀሪያው ዙር ግንባታ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል፡፡

በመቅደስ አስፋው