የሀገር ውስጥ ዜና

ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሽኝት ተደረገ

By Hailemaryam Tegegn

June 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የቀድሞ ሰብሳቢ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሽኝት ተደረገላቸው።

በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ኃላፊነቱን የተረከቡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰን ጨምሮ የቦርዱ አባላትና የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የቀድሞዎቹ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ዋልታ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተዋህደው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ከመሰረቱበት ጊዜ አንስቶ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው አገልግለዋል።

በዚህም ውህደቱን ስኬታማ ከማድረግ ጀምሮ አዲሱ ተቋም ጠንካራ ሚዲያ እንዲሆን የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ሚኒስትሯ በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላከናወኗቸው ስራዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመደባቸው ይታወቃል።

በሔብሮን ዋልታው