የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ተስፋ የሚለመልመው በሰለጠነ የፖለቲካ አውድ ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

By Hailemaryam Tegegn

June 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ ተስፋ የሚለመልመው በሰለጠነ የፖለቲካ አውድ ነው አሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር አካሂዷል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እውን የሚሆነው በተቋማት ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በዜጎች በሳል ተሳትፎ ጭምር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን በመስጠት ለምርጫው ስኬታማነት ከፍተኛ ሚና መወጣታቸውን ገልጸው፥ የኢትዮጵያ ተስፋ የሚለመልመው በሰለጠነ የፖለቲካ አውድ ነው ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሲቪል ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በቅድስት አባተ