አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል የሰላም ስምምነት ዛሬ ይፈረማል አሉ።
ትራምፕ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ቁልፍ የመርከቦች መስመር የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ ለሁሉም ክፍት ይሆናል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኢራን የስምምነት ፊርማ የሚደረግበትን ትክክለኛው ቀን ይህ ነው ባትልም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚደረግ አስታውቃለች።
ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱ እንደሚደረግ ቢገልጹም በሁለቱም በኩል የሚያስማማ ትክክለኛው ቀን አልታወቀም።
አሜሪካ እና ኢራንን እያደራደረች የምትገኘው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍ ትናንት ጦርነቱን ለማስቆም የሚያስችለው የሰላም ስምምነት በሚቀጥሉት 24 ሰዓት ውስጥ ይፈረማል ማለታቸው ይታወሳል።
በብርሃኑ አበራ