አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የጤና ተቋማትን አቅም በማሳደግ እና በዘመናዊ የሕክምና ግብዓት በማሟላት እንዲሁም በቴክኖሎጂ በማደራጀት ባለፉት ጥቂት ዓመታት እጅግ ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ የተሰሩ የጤና ልማት ተግባራት አክሞ የማዳን አቅምን አሳድገዋል፡፡
በዚህም ከተማዋን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት የተከናወኑ የጤና መሰረተ ልማት ስራዎች፣ ባለፉት 100 ዓመታት የነበረውን የጤና ተቋማት አቅም ከእጥፍ በላይ ማሳደግ ተችሏል።
የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግ ከተከናወኑ ሥራዎች፦
👉 የላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ 👉 የአበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ሆስፒታል፤ 👉 በዘውዲቱ ሆስፒታል ውስጥ የተገነባው የዘውዲቱ የህክምና ልህቀት ማዕከል፤ 👉 የሚኒሊክ ፎረንሲክና ስነ ምረዛ ምርመራ ማዕከል፤ 👉 የምኒሊክ የአይን ህክምና ማዕከል፤ 👉 የራስ ደስታ ሆስፒታሎች ውስብስብና ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
እንዲሁም በ21 ጤና ጣቢያዎች የኦፕሬሽን ማዋለድ አገልግሎት (C/S Delivery) የተጀመረ ሲሆን÷ ይህም ለእናቶች ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተለያዩ የጤና እክሎችንና ሞትን ለመቀነስ አስችለዋል።
በ2013 ዓ.ም የተገነባው የአበበች ጎበና እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል 400 አልጋዎችን የያዘና የእናቶችና ህጻናትን ጤና አገልግሎት አሰጣጥን በእጥፍ በማሳደግ በወር ከአንድ ሺህ በላይ የወሊድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል፤ ዘመኑን የዋጀ ባለ 4 ወለል የአይን ህክምና ማዕከል ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን÷ ይህም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ተገልጋዮችን ለማስተናገድ ጭምር አቅም የፈጠረ መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።
በ2017 ዓ.ም ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የተመረቀው እጅግ ዘመናዊ የህጻናት የአንጎልና ህብረሰረሰር ቀዶ ህክምና የልህቀት ማዕከል ከከተማ አልፎ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ህጻናት አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡
በተጨማሪም በዚያው ሆስፒታል በ320 አልጋዎች የተደራጀው የባለ8 ወለል ሕንጻ የላቀ ህክምና ተቋም የሆስፒታሉን ነባር አቅም በዕጥፍ አሳድጎታል።
አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማእከል የማድረግ ራእይን ለማሳካት ነባርና አዲስ ጤና ተቋማትን አቅማቸውን በማሳደግ እና በዘመናዊ የህክምና ግብአት በማሟላት እንዲሁም በቴክኖሎጂ በማደራጀት ባለፉት ጥቂት አመታት እጅግ ውጤታማ እና ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።
የጤና ጣቢያዎችንም አቅም በማሳደግ በጤና ጣቢያዎች ደረጃ ያልነበሩ አዲስ አገልግሎቶችን (የኬሞቴራፒ፤ በኦፕሬሽን ማዋለድ፤ ፓሊየቲቭ ኬር፤ የአይን ህክምና፤ የስነ አእምሮ ህክምና፤ የጥርስ ህክምና ቀዶ ህክምና እና ሌሎችን) እንዲጀመሩ መደረጉ ለህብረተሰቡ በተቀላጠፈ እንዲያገኝ እንዲያገኝ አስችሏል ፡፡
እንዲሁም አክሞ ማዳን ብቻም ሳይሆን በሽታን በመከላከል ውጤታማ የሆኑ የቤተሰብ ዕቅድ፤ የቅድመወሊድ እንዲሁም የወሊድ አገልግሎትን፥ የእናቶች ሞት መቀነስ፥ የጨቅላ ህፃናት ሞት መቀነስ፥ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች ተጠናክረው እየተተገበሩ ነው።
የማህፀን በር ካንሰር ከመከላከል እንዲሁም ወቅታዊ ምላሽ ከመስጠት አንጻር የቅድመ ምርመራና ምክር እንዲሁም የህክምና አገልግሎት አቅምን በማሳደግ በየአመቱ እስከ 90 ሺህ ሴቶችን ያለምንም ክፍያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
በቀጣይም በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ የሚገነቡ ወደ ውጭ ሀገር የሚደረጉ የህክምና ጉዞዎችን የሚያስቀሩ፥ በዘመኑ ቴክኖሎጂ የተደራጁ የህክምና ተቋማት በልዩ ትኩረት እየተስራ ሲሆን አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ እውን እየሆነ ይገኛል።