አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና የሰላም አማራጭ ተቀብለው ወደ ማህበረሰቡ ከተቀላቀሉ አካላት ጋር እየተወያየ ነው።
ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን በምክክር ሂደቱ ለማካተት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ቀጥለዋል፡፡
ታጣቂዎቹ ለሰላም ቦታ ሰጥተውና ጥያቄዎቻቸውን ቀርፀው ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ለማስረከብ ዝግጁ በመሆናቸው የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
የሚያዋጣው መንገድ ኢትዮጵያዊያን ፊት ለፊት ተገናኝተው የሀሳብ የበላይነትን ሲያረጋግጡ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፥ እነዚህ ኃይሎች ለሀሳብ ቅድሚያ ሰጥተው አጀንዳዎቻቸውን ለማካፈል በመገኘታቸው አመስግነዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ