ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሁለት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚከፈተው የሆርሙዝ ሰርጥ…

By Melaku Gedif

June 17, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሆርሙዝ ሰርጥ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ሙሉ በሙሉ ክፍት ይሆናል አሉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ።

አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ማቆም የሚያስችላቸውን ስምምነት በመጪው ዓርብ እንደሚፈራረሙ ይታወቃል።

በስምምነቱ መሰረት በዓለም ወሳኙ የነዳጅ ዘይት መተላለፊያ መስመር የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ እንደገና ይከፈታል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህንን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሁን ላይ የሆርሙዝ ሰርጥ በከፊል ክፍት እንደሆነ አንስተው ÷ በቀጣይ ቀናት ሙሉ በሙሉ ክፍት ይሆናል ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከኢራን ጋር የተደረሰው የሰላም ስምምነት ወሳኝና በጣም ጠንካራ እንደሆነ በተደጋጋሚ እየገለጹ ነው።

ዛሬም የስምምነቱ ሙሉ ሃሳብ ምን እንደሆነ ማንም አያውቅም፤ ነገር ግን በጣም ጠንካራ ነው ማለታቸውን ኤንቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

አሜሪካ፣ እስራኤልና ኢራን በገቡበት ጦርነት ምክንያት ቴህራን የሆሙዝ ሰርጥን በተደጋጋሚ በመዝጋቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተግዳሮት ሲከሰት ቆይቷል።

በብርሃኑ አበራ