አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 730 ሺህ 310 ወጣቶች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሳተፋሉ አለ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አያሌው ከይሳ እንዳሉት÷ ከዚህ በፊት በክልሉ በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በርካታ ውጤት ተመዝግበዋል።
በዚህ ዓመት የወጣቶችን ጉልበት፣ ዕውቀትና ጊዜ በማቀናጀት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል።
በዚህም ከ897 ሚሊየን ብር የሚገመት ሀብት ከመንግሥት ካዝና ማዳን እንደሚቻል መግለጻቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።
ከ71 ሚሊየን በላይ ችግኞችን መትክል፣ ከ1 ሺህ 80 በላይ ቤቶችን መገንባትና ማደስን ጨምሮ በ14 ዋና ዋና የአገልግሎት መስኮች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሰጥም አብራርተዋል።