አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች መካከል 121 ተጨማሪ የምርጫ ውጤቶች ፀድቀዋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
በዚህም ቦርዱ 34 የሕዝብ ተወካዮች እና 87 የክልል ምክር ቤት ውጤቶችን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡
ዛሬ ይፋ የተደረጉት በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የምርጫ ክልሎች ውጤቶች ናቸው፡፡
በፍቅርተ ከበደ