አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ‘ተስፋን እንትከል’ በሚል መሪ ሀሳብ በመዲናዋ 8ኛውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡
ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የከተማዋ የአረንጓዴ ሽፋን በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 2 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 24 በመቶ ማሳደግ ተችሏል፡፡
አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ ጽዱ እና ውብ በማድረግ ሂደት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፥ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በከተማዋ ከ6 ሚሊየን በላይ ችግኝ እንደሚተከል ጠቁመዋል።
ከዛሬ ጀምሮ በከተማዋ የሚተከሉ ችግኞች ፀድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ ከንቲባዋ አሳስበዋል።
በይስማው አደራው