አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ ግብር እያካሄደ ይገኛል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬን ጨምሮ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ታድመዋል፡፡
የምርጫው ውጤት ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በአንዱዓለም ተስፋዬ