አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አካታችነትን ዋና መርህ በማድረግ ሰርቷል አሉ የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ።
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በምርጫው ለመጀመሪያ ጊዜ የዲጂታል የመራጮችና እጩዎች ምዝገባ ሥርዓትን ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
በምርጫው የቅሬታ አፈታት ሒደት ቅልጥፍና እንዲኖረው፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሕግ መሰረት እንዲያገኝ፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በምርጫ የተሻለ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ የሕግና የአሰራር ማሻሻያዎችን መደረጋቸውን አንስተዋል።
ቦርዱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አካታችነትን ዋና መርህ በማድረግ እንደሰራ አስረድተዋል።
ቦርዱ ሥራውን በሚሰራባቸው አካባቢዎች የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃትን መከላከያ ፖለሲ ተግባራዊ እንዳደረገ አንስተዋል።
በምርጫ ሒደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት ለምርጫው ስኬታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ ለነበራቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በብርሃኑ አበራ