የሀገር ውስጥ ዜና

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Yonas Getnet

June 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፓርቲያቸው ብልፅግና በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፋቸው ልባዊ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡

በማሌዥያ መሪዎች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ጉብኝት በአዲስ አበባ ማድረጋቸውን አስታውሰው÷ በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መወያየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በነበረው ውይይት ታዳጊ የደቡብ ሀገራት እኩልነታቸውን እንዲያረጋግጡ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ምክክር ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

ማሌዥያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ለምታደርገው ትብብር ኢትዮጵያ አስፈላጊ መሆኗን ገልጸው÷ ትብብሮችን በማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡