የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን ዲኤችሲ- 6 ትዊን ኦተር ክላሲክ 300 -ጂ አውሮፕላን ተረከበ

By Yonas Getnet

June 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ‘ዴ ሃቪላንድ ካናዳ’ ለመረከብ ካቀዳቸው ሁለት የ ’ዲኤችሲ- 6 ትዊን ኦተር ክላሲክ 300 -ጂ’አውሮፕላኖች መካከል የመጀመሪያውን በዛሬው ዕለት ተረክቧል፡፡

አዲስና ልዩ የሆኑት አውሮፕላኖቹ የአየር መንገዱን የውስጥና የቀጣናዊ በረራ አገልግሎት ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም ለቱሪዝም ዘርፍ እንቅስቃሴዎች፣ ለአየር ላይ የቅኝትና ጥናት ሥራዎች፣ ለአየር አምቡላንስ አገልግሎትና ለሌሎች መሰል ተግባራት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖራቸው አየር መንገዱ ገልጿል።

አውሮፕላኖቹ የአየር መንገዱን የተለያዩ የገበያ ፍላጎቶች በብቃት እና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላትና ተደራሽነቱን ለማስፋፋት ያለውን አቅም ይበልጥ እንደሚያጠናክሩም ተጠቁሟል።