የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል ከ18 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Mikias Ayele

June 23, 2026

‎‎አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል በበጀት ዓመቱ 11 ወራት የማዘጋጃ እና መደበኛ ገቢን ጨምሮ ከተለያዩ የገቢ አማራጮች 18 ቢሊየን 880 ሚሊየን ብር ገቢ ተሰብስቧል።

የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን የ2018 እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሂዷል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደምሴ እሳቱ በወቅቱ እንዳሉት፤ የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ ምጣኔ በየዓመቱ በአማካኝ የ44 በመቶ እድገት እያሳየ መጥቷል።

በፌደራል እና በክልል ደረጃ ከተከናወኑ የገቢ አዋጅ ማሻሻያዎች ባሻገር በባለድርሻ ተቋማት መካከል የተፈጠረው ቅንጅታዊ አሰራር እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ባህል መዳበሩ ለተመዘገበው ውጤት ምክንያት ስለመሆኑ አንስተዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ የአደረጃጀት ዘረፍ ሀላፊ አሸናፊ ኤልያስ በበኩላቸው፤ የክልሉ ኢኮኖሚ ሊያመነጭ የሚችለውን ሀብት በአግባቡ እንዲሰበሰብ አመራሩ የተጣለበትን ኃላፊነት ተወጥቷል ብለዋል፡፡

የገቢ ማሰባሰብ ተግባሩ ከብልሹ አሠራር በፀዳ አኳኋን በባለቤትነት መንፈስ መተግበሩን ተናግረዋል።

በነገዎ ብዙነህ