ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኢራን ለቀድሞው መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊኻሜኒ ቀብር ሥነ ስርዓት ሶስት የበዓል ቀናት አወጀች

By Mikias Ayele

June 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ለተገደሉት የቀድሞው መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ የቀብር ሥነ ስርዓት ሶስት የበዓል ቀናት አውጃለች፡፡

የአስከሬን ሽኝቱ በፈረንጆቹ ሐምሌ 4 በቴህራን የሚደረግ ሲሆን፥ የቀብር ሥነ ስርዓታቸው ደግሞ በፈረንጆቹ ሐምሌ 9 በተወለዱበት ማሻድ ከተማ ይፈፀማል መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል።

አሜሪካ እና እስራኤል በፈረንጆቹ የካቲት 28 በኢራን ላይ በፈጸሙት የሚሳኤል ጥቃት የ86 ዓመቱ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊኻሜኒ መገደላቸው ይታወቃል።

አያቶላህ አሊኻሜኒ በፈረንጆቹ በ1979 የተካሄደውን የኢራን እስላማዊ አብዮት በመምራት የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከመሠረቱ የሺአ ሙስሊሞች ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ አንዱ ነበሩ፡

በኢራን ንጉሳዊ ሰርዓት ከወደቀ በኋላ ወደ መሪነት የመጡት አያቶላህ ሩሆላህ ኾሜኒ ከ10 ዓመታት በኋላ መሞታቸውን ተከትሎ ስልጣነ መንበሩን የተረከቡት አያቶላህ አሊ ኾሚኒ አራንን ከ35 ዓመታት በላይ መርተዋል።

በሚኪያስ አየለ