የሀገር ውስጥ ዜና

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Hailemaryam Tegegn

June 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብልጽግና ፓርቲ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ፣ ዘርፈ ብዙና ለዘመናት የቆየ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስታውሰው፥ ስትራቴጂያዊ አጋርነታችንን እና በሕዝቦቻችን መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር የበለጠ ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡