የሀገር ውስጥ ዜና

የኳታሩ ኤሚር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Mikias Ayele

June 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ በማሸነፉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሼክ ታሚም ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልጽግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፋቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለብልጽግና ፓርቲ መልካም የስራ ዘመን የተመኙት ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ÷ በኢትዮጵያ እና ኳታር መካከል ያለው የሁለትሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡