አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የሚዛን አማን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
በክልሉ ሚዛን አማን ከተማ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው ማዕከሉ የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተገልጿል።
በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳደሩ የሚዛን አማን ኮሪደርና ስማርት ፖል እንዲሁም የሚዛን አማን መናኸሪያን ጨምሮ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶችን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
በተስፋየ ምሬሳ