የሀገር ውስጥ ዜና

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና አፍሪካ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

June 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በአፍሪካ ትብብር ላይ ያተኮረው “ሂሊ ዲያሎግ አፍሪካ ኤዲሽን” የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፖሊሲ አውጪዎች፣ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የወደብና መሠረተ ልማት ትስስር፣ ወሳኝ ማዕድናትና ቴክኖሎጂ፣ የምግብ ደህነነትና ታዳሽ ኃይል እንዲሁም አዳዲስ የንግድ አጋርነት ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

መድረኩ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከኤምሬትስ የስልታዊ ጥናቶችና ምርምር ማዕከል እንዲሁም ከአንዋር ጋርጃሽ ዲፕሎማቲክ አካዳሚ በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዓለምሰገድ አሳዬ