የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ትሰራለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Hailemaryam Tegegn

June 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር በቁርጠኝነት ትሰራለች አሉ፡፡

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ ብልጽግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ያስተላለፉት መልዕክት የሁለቱን ሀገራት የእህትማማችነት መንፈስ የሚያንጸባርቅ መሆኑን ጠቅሰው፥ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በእድገት ጎዳና ላይ እንደሚገኙ ገልጸው፥ ሁሉን አቀፍ እድገትን እውን ለማድረግ በጋራ መቆማቸውን አንስተዋል፡፡