በዱራሜ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጀመረ

By Yonas Getnet

June 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዱራሜ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ መርቀው ሥራ ያስጀመሩት ማዕከሉ በመጀመሪያ ዙር በ6 ተቋማት 20 አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ርዕሰ መስተዳድሩ በማዕከሉ የተጀመረውን አገልግሎት ተዘዋውረ ተመልክተዋል።