የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

By Mikias Ayele

June 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል፡፡

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የአቅመ ደካማ ወገኖች የቤት ግንባታ ማስጀመር ስራ ተከናውኗል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በወቅቱ እንዳሉት÷ በጎነት የጤናማ ማህበረሰብ ዋነኛ መገለጫ ነው።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ የክልሉ ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ጠቅሰው፤ በተለይ አቅመ ደካሞች ተገቢውን ድጋፍ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ይበልጥ እንዲጠናከር አጋሮች፣ ወጣቶች፣ የመንግሥት ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ትብብራቸውን አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ አመልክቷል።