የሀገር ውስጥ ዜና

የፈተና ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)

By Mikias Ayele

June 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) የፈተና ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል አሉ።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 በበይነ መረብና በወረቀት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ የፈተና ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በፈተና ሂደት ወቅት ፈተና ለመስረቅም ይሁን ለማሰረቅ የሚሞክሩ አካላት ላይ ጥብቅ ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅሰው÷ ለፈተናው ስኬታማነት ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ በበኩላቸው÷ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የጸጥታ ዘርፉ ተገቢውን ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።

የፈተናውን ሂደት በታሰበው አግባብ በስኬት እንዲጠናቀቅ በታማኝነትና በትብብር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናውን ለመውሰድ ከ563 ሺህ በላይ ተፈታኞች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡