የሀገር ውስጥ ዜና

35 ‘A+’ በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳልያ የተሸለመው የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ

By Hailemaryam Tegegn

June 27, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተማሪ የሆነው አንቲ ምትኩ 35 ‘A+’ በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳልያ ተሸልሟል፡፡

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 679 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች መካከል የሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተማሪ የሆነው አንቲ ምትኩ 3 ነጥብ 99 ውጤት የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል።

ከ49 ኮርሶች 35 ‘A+’ እና 13 ‘A’ እንዲሁም 1 ‘A-‘ በማምጣት ነው የዩኒቨርሲቲው 8ኛ ዙር ምረቃ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ የሆነው።

ተማሪ አንቲ ምትኩ በቀጣይም በተማረበት ሙያ ለሀገሩ የራሱን አሻራ ለማኖር እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡

በዩሱፍ ጁሃር