አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ዩኒቨርሲቲ 3 ነጥብ 9 ወጤት በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀችው ዶ/ር ነቢላ ሺፋ በእያንዳንዱ ርምጃ ተስፋ ሳትቆርጥ በጽናት ለዓላማዋ መትጋቷ ውጤታማ እንዳደረጋት ተናግራለች፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ2ሺ 900 በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል ትምህርቷን ስትከታተል የቆየችው ዶ/ር ነቢላ ሺፋ ከፍተኛ ወጤት በማምጣት የወርቅ ተሸላሚ ሆናለች፡፡
በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ የውስጥ ፍላጓቷ ለሚያደላለት የጥርስ ህክምና ትምህርት ሙሉ ጊዜዋን ያለመታከት በመስጠቷ በከፍተኛ ማዕረግ ለመመረቅ እንዳበቃት ተናግራለች፡፡
በአጠቃላይ ሦስት ሽልማቶች የተበረከቱላት ሲሆን፥ ወደፊት በዚህ የህክምና ዘርፍ ሀገርን ለማገልገል ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች፡፡
ዶ/ር ነቢላ ሺፋ ለዚህ ስኬት እንድትበቃ እገዛ ያደረጉላትን መምህራንና ቤተሰቦቿን አመስግናለች፡፡
በወርቅአፈራው ያለው