አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በ2026ቱ የእስያ ጭነት፣ ሎጂስቲክስና አቅርቦት ሰንሰለት የአፍሪካ ምርጥ የአየር ጭነት አጓጓዥ አየር መንገድ በመባል ተሸላሚ ሆኗል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ መሰረተ ልማቶች፣ ስልታዊ ጥምረቶች እንዲሁም አዳዲስ የሎጂስቲክስ አሰራሮች በመታገዝ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ እና የንግድ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ካርጎ ሽልማቱን ያገኘው በዘርፉ ባለድርሻ አካላትና በደንበኞች በተሰጠ ከፍተኛ ድምፅ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
አየር መንገዱ ይህ ስኬት ዕውን እንዲሁን ላስቻሉ አጋሮች፣ ደንበኞች እንዲሁም ሰራተኞች ምስጋና አቅርቧል፡፡