የሀገር ውስጥ ዜና

ደብረ ብርሃንና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ

By Yonas Getnet

June 28, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ደብረ ብርሃን እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ለ20ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 807 ተማሪዎች ነው ያስመረቀው፡፡ ‎ ተመራቂዎች ‎በጤና፣ በምህንድስና፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በግብርናና ተፈጥሮ ሃብት እንዲሁም በሕግ እና በሌሎች መስኮች የሠለጠኑ ናቸው።

‎የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ዩኒቨርሲቲው የተግባር ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ በተግባር የሰለጠኑ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው። ‎ ‎ተማሪዎች ቴክኖሎጂን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በማድረግ ጊዜውን የሚመጥኑ ተማሪዎችን እያፈራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 279 ተማሪዎች አስመርቋል።

በኤልያስ ሹምዬ