አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፓራጓይ የ4 ጊዜ ሻምፒዮኗን ጀርመንን በመለያ ምት በማሸነፈ 16ቱን ተቀላቅላለች።
በጨዋታው ኢንሲሶ ፓራጓይን ቀዳሚ ሲያደርግ ካይ ሀቨርትዝ ደግሞ ጀርመንን አቻ አድርጓል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና ተጨማሪ 30 ደቂቃውን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቅቀዋል፡፡
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም ፓራጓይ የ4 ጊዜ ሻምፒዮኗን ጀርመንን 4 ለ 3 በማሸነፍ 16ቱን መቀላቀል ችላለች፡፡
ፓራጓይ በቀጣዩ ዙር ጨዋታ የፈረንሳይ እና የስዊድንን አሸናፊ የምትገጥም ይሆናል።