ስፓርት

ቼልሲ ጣሊያናዊውን ተከላካይ ማርኮ ፓሌስትራን አስፈረመ

By abel neway

July 01, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቼልሲ ጣሊያናዊውን የአታላንታ የክንፍ ተከላካይ ማርኮ ፓሌስትራን አስፈርሟል፡፡

የ21 አመቱ ፓሌስትራ የዣቪ አሎንሶ የመጀመሪያ ፈራሚ በመሆን ስታንፎርድ ብሪጅ የደረሰ ሲሆን፤ በ47 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ቼልሲን ተቀላቅሏል።

ተጨዋቹ ለስድስት ዓመታት በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ለመቆየትም ኮንትራት ፈርሟል፡፡

ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በውሰት በካግሊያሪ ያሳለፈው ማርኮ ፓሌስትራ፤ የሴሪ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተከላካይ በመሆንም መመረጡ ይታወሳል፡፡