ፋና ስብስብ

የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል

By Yonas Getnet

July 05, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በዘመን አይሽሬ እና በባሕላዊ ስራዎቿ የብዙዎችን ልብ የማረከችው አንጋፋዋ ድምፃዊትና የዜማ ደራሲ ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

በኪነ ጥበብ ህይወቷ በርካታ የማይረሱ ድንቅ ስራዎችን ለህዝብ በማበርከት ታላቅ ባለውለታ የነበረችው አርቲስቷ ስኬታማ የጥበብ ጉዞ ነበራት።

ድምጻዊት ራሔል ዮሐንስ የሁለት ወንድና የአራት ሴት ልጆች እናት ነበረች።

የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ነገ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደብረ ምህረት ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴደራል ቀን 8 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።