ስፓርት

ቶተንሃም ሆትስፐር ሳንድሮ ቶናሊን አስፈረመ

By Melaku Gedif

July 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር ጣሊያናዊውን ተጫዋች ሳንድሮ ቶናሊን ከኒውካስል ዩናይትድ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር የክለቡን የዝውውር ክብረ ወሰን በመስበር በ100 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ተጫዋቹን የግሉ አድርጓል፡፡

የ26 ዓመቱ ተጫዋች በሰሜን ለንደኑ ክለብ እስከ ፈረንጆቹ 2032 ድረስ የሚያቆየውን ውል ነው የተፈራረመው፡፡

ሳንድሮ ቶናሊ በፈረንጆቹ 2023 ኒውካስል ዩናይትድን የተቀላቀለ ሲሆን÷ 110 ጨዋታዎችን አድርጎ 10 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

ተጫዋቹ በኒውካስል ዩናይትድ ቆይታው የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ማሳካቱ ይታወሳል፡፡